በቻይና በተካሄደው ዓለም አቀፍ 13ኛው የዤንግዡን የሻዎሊን ውድድር ላይ ኢትዮጵያን የወከሉ ማስተሮች በቡድን የብር ሜዳሊያ በማምጣት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በውድድሩ መጨረሻ ቀን በተደረገው ፋክክር ሲኒየር ማስተር ሰሚር ናስር በብሮድ ስዎርድ የነሀስ ሜዳሊያ፤ ማስተር ኢማዱዲን ሰዒድ በከጀል የነሀስ ሜዳልያ ያመጡ ሲሆን በድምሩ ልዑካን ቡድናችን በነጠላ አርት ውድድር አንድ ብር እና አራት ነሀስ እንዲሁም በቡድን አርት ውድድር የብር ሜዳሊያ በማምጣት ውድድራቸውን በጥሩ ውጤት አጠናቀዋል።